
ADDISMALEDA.COM – የዱባይ የኢኮኖሚና ቱሪዝም ዲፓርትመንት የአፍሪካ ዓለም ዐቀፍ ኦፕሬሽኖች ዳይሬክተር ስቴላ ፉቡራ በኢትዮጵያ ይገኛሉ
ዕረቡ ሐምሌ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዱባይን የዓለም ኢኮኖሚ ዋና ማዕከል፣ የኢንቨስትመንት እንብርትና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየሠራ የሚገኘው፤ የዱባይ የኢኮኖሚና ቱሪዝም ዲፓርትመንት (DET) የአፍሪካ ዓለም ዐቀፍ ኦፕሬሽኖች ዳይሬክተር ስቴላ ፉቡራ በኢትዮጵያ ይገኛሉ።
ስቴላ በአፍሪካ ውስጥ የዱባይ ቱሪዝም አገልግሎትን እንዲያስተዳድር ኀላፊነት ከተሰጠው “ሪቬክሴል ሊሚትድ” (Rivexcel Limited) ከተሰኘው፤ የናይጄሪያ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቶኒ ፕሪንስዊል ጋር በጋራ በመሆን ነው በኢትዮጵያ የተገኙት።
የዳይሬክተሯ የጉብኝት ዓላማም፤ የዱባይ የኢኮኖሚና ቱሪዝም ዲፓርትመንት (DET) የቱሪዝም ዘርፎች ላይ እየሠራ የሚገኘውን ሥራ ለማስተዋወቅና በኢትዮጵያ ባሉ የቱሪዝም አማራጮች ላይ በመወያየት ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እና አጋርነት ለመፍጠር ሲሆን፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚገኙ የጉዞ ወኪሎች እና አስጎብኚ ድርጅቶች ንግዳቸውን እንዲያሻሽሉ ድጋፍ እና ሥልጠና የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው።
Read More @ addismaleda.com
Reviews
0 %